Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 7
Listen to find out how to ask if someone has any brothers or sisters.
አንድ ሰው ወንድሞች ወይንም እህቶች እንዳሉት እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
ክፍለጊዜያት 7 ነጥብ።
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
Have you got any brothers or sisters?
Listen to find out how to ask if someone has any brothers or sisters.
አንድ ሰው ወንድሞች ወይንም እህቶች እንዳሉት እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊተዋቸው የማይቻላቸውን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation በደህና መጡ። ሐና እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሰዎች ወንድሞች ወይንም እህቶች እንዳሏቸው ወይንም እንደሌሏቸው እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ይማራሉ።
እስኪ ሁለት ሰዎች ወንድሞች ወይንም እህቶች መኖር ያለመኖራቸውን ሲነጋጋሩ ያዳምጡ።
Tina
Have you got any brothers or sisters?
John
Yes, I’ve got two sisters. How about you?
Tina
I’ve got a brother.
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ቲና ጆንን ‘ወንድሞች ወይንም እህቶች አሉህ ወይ’ ‘Have you got any brothers or sisters?’ ስትል ነው የጠየቀችው። አስታውሱ ሁሌም ‘have you got…’. ብለን ስንጠይቅ ‘any’ የሚለውን ቃል አብረን እንጠቀማለን። ያዳምጡና ሐረጉን ይድገሙ።
Insert
Have you got any brothers or sisters?
Have you got any brothers or sisters?
ከዚያ ጆን ‘ሁለት እህቶች አሉኝ’ ‘I’ve got two sisters.’ በማለት መልሷል። ‘I’ve got’ እና ‘I have’ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው። እናም ደግሞ ከአንድ በላይ እህት ሲኖረን ‘sister’ በሚለው ቃል ላይ ‘S’ ን እንጨምራለን። ነገር ግን አንድ እህት ብቻ ከሆነ ያለን በ ‘sister’ ላይ ‘S’ን አንጨምርም። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
Insert
Yes, I’ve got two sisters.
Yes, I’ve got two sisters.
ከዚያም ጆን ‘አንቺስ?’ ‘How about you?’ በማለት ተመሳሳዩን ጥያቄ አዙሮ ጠይቋታል። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
Insert
How about you?
How about you?
ከዚያም ቲና ‘አንድ ወንድም አለኝ’ ‘I’ve got a brother.’ ብላ መለሰች። ‘a brother’ ማለት ‘አንድ ወንድም’ ማለት ነው። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
Insert
I’ve got a brother.
I’ve got a brother.
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች ምን ያህል ወንድሞች እና እህቶች እንዳሏቸው ሲጠያየቁ በማዳመጥ እርስዎ ሲሉ የቆዩቱን ይፈትሹ።
Have you got any brothers or sisters?
Yes, I’ve got a sister. How about you?
I’ve got two brothers and a sister.
Have you got any brothers or sisters?
Yes, I’ve got a sister and a brother. How about you?
I’ve got two sisters.
Have you got any brothers or sisters?
Yes, I’ve got two brothers. How about you?
I’ve got two sisters and a brother.
በጣም ግሩም! እስኪ እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ወንድሞች ወይንም እህቶች አሉህ?
Have you got any brothers or sisters?
አዎ፥ ሁለት እህቶች አሉኝ።
Yes, I’ve got two sisters.
አንችስ?
How about you?
አንድ ወንድም አለኝ።
I’ve got a brother.
በጣም ጥሩ፤ እስኪ አሁን የዛሬዎቹን አገላለፆች ለማስተዋል ሙሉውን ውይይት ያዳምጡ።
Tina
Have you got any brothers or sisters?
John
Yes, I’ve got two sisters. How about you?
Tina
I’ve got a brother.
በጣም ጥሩ! አሁን በእንግሊዝኛ ሰዎች ምን ያህል ወንድሞች እና እህቶች እንዳሏቸው መጠየቅ ይችላሉ። የተማሩትን ነገር መለማመድን አይዘንጉ። ጓደኛ ይፈለጉና ምን ያህል ወንድሞች እና እህቶች እንዳሏቸው በእንግሊዝኛ በመጠየቅ ልምምድ ያድርጉ። ለተጨማሪ የዕለት ተዕለት እንግሊዝኛ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ! Bye!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ የተማሩትን ነገር ይፈትሹ።
Have you got any brothers or sisters?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ድጋፍ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ፍንጭ
ይህ ቃል ሶስት ሆሄያት አሉት።Question 1 of 3
ድጋፍ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ፍንጭ
ምን ያህል? አንድ ወይንስ ከዚያ በላይ?Question 2 of 3
ድጋፍ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ፍንጭ
'አንድ' የሚል ትርጉም ያለው አንድ ሆሄQuestion 3 of 3
Excellent! Great job! መጥፎ እድል ነጥብ አስመዝግበዋል :
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ይበልጥ ጠቃሚ የሆኑ አገላለፆችን የምንማርበትና የመስማት ክህሎትን የምናዳብርበትን ቀጣዩ የአስፈላጊ እንግሊዘኛ ክፍለ ጊዜን ይከታተሉ።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Have you got any brothers or sisters?
ወንድሞች ወይንም እህቶች አሉህ/አሉሽ?Yes, I’ve got a sister.
አዎ፥ አንዲት እህት አለችኝ።Yes, I’ve got a brother.
አዎ፥ አንድ ወንድም አለኝ።
How about you?
አንተስ/አንችስ?