Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 24
Listen to find out how to talk about different meals.
በተለያዩ ሰዓቶች ስለሚበሉ የምግብ ምድቦች እንዴት መናገር እንደሚቻል ለማወቅ ማዳመጥዎን ይቀጥሉ።
ክፍለጊዜያት 24 ነጥብ።
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
Different meals
Listen to find out how to talk about different meals.
በተለያዩ ሰዓቶች ስለሚበሉ የምግብ ምድቦች እንዴት መናገር እንደሚቻል ለማወቅ ማዳመጥዎን ይቀጥሉ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያንን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ዘሩባቤል እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሰዎች ምን እንደሚመገቡ መጠየቅን ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች ብዙ ጊዜ ስለሚመገቧቸው የምግብ ዓይነቶች ሲነጋግሩ ያዳምጡ።
Phil
Hi Sian. What do you eat for breakfast?
Sian
I usually eat porridge for breakfast. What about you?
Phil
I always eat fruit.
ዘሩባቤል
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያው ተናጋሪ ሁለተኛዋን ተናጋሪ ቁርስ ‘breakfast’ ምን እንደበላች ነው የጠየቃት። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
What do you eat for breakfast?
ዘሩባቤል
ሁለተኛዋ ተናጋሪ ‘usually’ አዘውትራ የምትመገበው ‘porridge’ ገንፎ መሆኑን መልሳለች። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I usually eat porridge for breakfast.
ዘሩባቤል
ክዚያ የመጀመሪያውን ተናጋሪ ተመሳሳይ ጥያቄ አቀረበችለት። አንድ ሰው የጠየቃችሁን ጥያቄ መልሳችሁ ለጠያቂው ማቅረብ ስትፈልጉ ‘What about you?’ አንተስ ወይንም አንችስ ማለት ትችላላችሁ። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
What about you?
ዘሩባቤል
የመጀመሪያው ተናጋሪ ‘always’ ሁልጊዜ ለቁርስ ‘fruit’ ፍራፍሬ እንደሚበላ ተናግሯል።
I always eat fruit.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ ያሉትን ለማጣራት የተለያዩ ሰዎች ስለተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ሲነጋገሩ ያዳምጡ።
ሮብ ‘lunch’ ለምሳ ‘fish stew’ የዓሳ ወጥ ይበላል። ኒኮል ደግሞ ‘chicken’ ዶሮ እና ‘rice’ ሩዝ ትበላለች።
Hi Rob. What do you eat for lunch?
I usually eat fish stew for lunch. How about you?
I usually eat chicken and rice.
ሄዘር ለራት የበግ ስጋ ‘lamb’ ስትበላ ኒክ ደግሞ አትክልት ‘vegetables’ ይመገባል።
Hi Heather. What do you eat for dinner?
I always eat lamb for dinner. What about you?
I usually eat vegetables.
ዘሩባቤል
እሽ፤ አሁን ደግመን እንሞክረው። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ይሰማሉ።
What do you eat for breakfast?
What do you eat for breakfast?
I usually eat porridge for breakfast.
I usually eat porridge for breakfast.
What about you?
What about you?
I always eat fruit.
I always eat fruit.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታውሱት እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ለቁርስ ምን ትበያለሽ?
What do you eat for breakfast?
ቁርስ አዘውትሬ የምበላው ገንፎ ነው።
I usually eat porridge for breakfast.
አንተስ?
What about you?
እኔ ሁሌም ፍራፍሬ ነው የምበላው።
I always eat fruit.
ዘሩባቤል
ግሩም! አሁን ምግብ ቤት ገብተው ምግብ በእንግሊዝኛ እንዴት ማዘዝ እንደሚችሉ ያውቃሉ። ለሲያን ምላሽ በመስጠትና የሚፈልጉትን በመናገር ይለማመዱ።
What do you eat for breakfast?
I always eat fruit.
ዘሩባቤል
አሁን መልስዎን ለማጣራት ሙሉውን ውይይት ያዳምጡ።
Phil
Hi Sian. What do you eat for breakfast?
Sian
I usually eat porridge for breakfast. What about you?
Phil
I always eat fruit.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤! አሁን ሰለምግብ ሰዓት እና ዓይነቶች በእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ችለዋል። የተማሩትን መለማመድ አይዘንጉ። ጓደኛ ይፈልጉና በእንግሊዝኛ ምግብ በማዘዝ ልምምድ ያድርጉ። ለተጨማሪ የዕለት ተዕለት እንግሊዝኛ በሚቀጥለው ዝግጅታችን ይጠብቁን።
Check what you’ve learned by putting the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል በማስቀመጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
የተለያዩ የምግብ ሰዓቶች/ምድቦች
3 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ድጋፍ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ፍንጭ
እኝህ ሰው ሌላን ሰው ቁርስ ምን እንደሚበሉ እየጠየቋቸው ነው።Question 1 of 3
ድጋፍ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ፍንጭ
እኝህ ሰው ብዙ ጊዜ ለቁርስ ገንፎ ይመገባሉ።Question 2 of 3
ድጋፍ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ፍንጭ
እኔ ሁሌም ______ ነው የምበላው።Question 3 of 3
Excellent! Great job! መጥፎ እድል ነጥብ አስመዝግበዋል :
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያንን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
What do you eat for breakfast?
ለቁርስ ምን ትበያለሽ/ ትበላለህ?
I usually eat ______ for breakfast.
ለቁርስ አዘውትሬ የምበላው ______ ነው።
I always eat ______.
እኔ ሁሌም ______ ነው የምበላው።
What about you?
አንተስ?/ አንችስ?
lunch
ምሳ
dinner
እራት
porridge
ገንፎ
fruit
ፍራፍሬ
fish stew
የአሳ ወጥ
chicken and rice
ዶሮ በሩዝ
lamb
የበግ ስጋ
vegetables
አትክልት