Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 39
Listen to find out how to ask about what people do in their spare time.
ሰዎች በትርፍ ጊዜያቸው ምን እንደሚያደርጉ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
ክፍለጊዜያት 39 ነጥብ።
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
What do you do in your spare time?
Listen to find out how to ask about what people do in their spare time.
ሰዎች በትርፍ ጊዜያቸው ምን እንደሚያደርጉ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይስሩ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ለማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ የሚያስፈልጉ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደምናቀርብበት Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሰዎች ምን እንደሚያደርጉ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች በትርፍ ጊዜያቸው ስለሚያከናውኗቸው ተግባሮች ሲጠያየቁ ያዳምጡ።
Sam
What do you do in your spare time?
Rob
I play the guitar in a band. What about you?
Sam
I like exercising.
ምህረተስላሴ
የተነጋገሩትን ለመረዳት ከተቸገሩ፤ አያስቡ። ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ሳም ሮብን በትርፍ ጊዜህ ‘in your spare time?’ የሚለውን ሐረግ ከምን ታደርጋለህ ‘What do you do…?’ ከሚለው ጋር አጣምራ ጠይቃዋለች። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
What do you do in your spare time?
ምህረተስላሴ
ከዚያም ሮብ የሙዚቃ ባንድ ውስጥ ጊታር እጫወታለሁ ‘I play the guitar in a band’ ብሎ መለሰ። ስለምንጫወታቸው የሙዚቃ መሳሪያዎች ለመናገር ‘play’ የሚባለውን ቃል እንጠቀማለን። ‘band’ የሙዚቃ ባንድ ማለት ነው።
play’
I play the guitar in a band.
ምህረተስላሴ
ከዚያም ሮብ አንችስ? በማለት ተመሳሳይ ጥያቄ ለሳም ሰንዝሯል።
What about you?
ምህረተስላሴ
በመጨረሻም ሳም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደምትወድ ተናገረች። ማድረግ የሚወዱትን ነገር ለመግለፅ
‘I like’ የሚለውን ከተጠቀምን በኋላ በ‘–ing’ የሚጨርስ ቃል እናስከትላለን። ለምሳሌ ፊልም ማየት የሚወዱ ከሆነ ‘I like watching movies’ ይላሉ። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I like exercising.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች ስለሚያዘወትሯቸው ስፖርቶች ሲወያዩ በማዳመጥ እርስዎ የተናገሩትን ይፈትሹ።
What do you do in your spare time?
I go fishing by the river. What about you?
I like playing sports.
What do you do in your spare time?
I play basketball with my friends. What about you?
I like meeting friends.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ ይህንን ደግመን እንሞከረው። የእንግሊዝኛውን አረፍተ ነገር ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
What do you do in your spare time?
What do you do in your spare time?
I play the guitar in a band.
I play the guitar in a band.
What about you?
What about you?
I like exercising.
I like exercising.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
በትርፍ ጊዜህ ምን ታደርጋለህ?
What do you do in your spare time?
የሙዚቃ ባንድ ውስጥ ጊታር እጫወታለሁ።
I play the guitar in a band.
አንችስ?
What about you?
አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እወዳለሁ።
I like exercising.
ምህረተስላሴ
በጣም ግሩም፤ አሁን ስዎች በትርፍ ጊዜያቸው ምን እንደሚያደርጉ መጠየቅ አውቀዋል። ለሳም ምላሽ በመስጠት ልምምድ ያድርጉ። ‘How about you?’ የተባለውን ተከታይ ጥያቄ ማቅረብን አይርሱ።
What do you do in your spare time?
I like exercising.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን አጠቃላይ ውይይቱን አንዴ ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Sam
What do you do in your spare time?
Rob
I play the guitar in a band. What about you?
Sam
I like exercising.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሰዎች በትርፍ ጊዜያቸው ምን እንደሚያደርጉ በእንግሊዝኛ መጠየቅ ችለዋል። ጓደኛ ይፈልጉና ምን ዓይነት ስፖርት እንደሚያዘወትሩ በእንግሊዝኛ በመጠየቅ ይለማመዱ። ለተጨማሪ የኢንሴንሻል ኢንግሊሽ መሰናዶ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!
Check what you’ve learned by putting the words in the correct order.
ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
በትርፍ ጊዜህ/ሽ ምን ታደርጋለህ/ጊያለሽ?
3 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
ድጋፍ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
ፍንጭ
‘Do’ የሚለው ቃል ሁለት ጊዜ ይመጣል።Question 1 of 3
ድጋፍ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
ፍንጭ
ከ 'like' በኋላ በ ‘-ing’ የሚያልቅ ቃል እንጠቀማለን።Question 2 of 3
ድጋፍ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
ፍንጭ
‘I play’ ብለው ይጀምሩ።Question 3 of 3
Excellent! Great job! መጥፎ እድል ነጥብ አስመዝግበዋል :
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
What do you do in your spare time?
በትርፍ ጊዜህ ምን ታደርጋለህ?I play the guitar in a band.
በሙዚቃ ባንድ ውስጥ ጊታር እጫወታለሁ።I like exercising.
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እወዳለሁ።I go fishing by the river.
ወደ ወንዝ ወርጄ ዓሣ ማጥመድ እወዳለሁ።I like playing sports.
ስፖርት እወዳለሁ።I play basketball with my friends.
ከጓደኞቼ ጋር እግር ኳስ እጫወታለሁ።What about you?
አንችስ?