Unit 1: How do I...
Select a unit
- 1 How do I...
- 2 Unit 2
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 9
Listen to find out how to make a phone call in English.
ስልክ ላይ በእንግሊዝኛ እንዴት ማውራት እንደሚቻል ለማወቅ ያዳምጡ።
Activity 1
How do I make a phone call?
እንዚህን ንግግሮች ማን ነው ሊላቸው የሚችለው፤ ደዋዩ ነው ወይስ ተደዋዩ?
| ደዋይ | ተደዋይ |
Hello?
Hello, is Melissa there, please?
Sorry, she's not here at the moment.
Can I take a message?
It's ok. I'll call back later.
Hello, can I speak to Melissa, please?
Yes. Who’s speaking, please?
It’s Peter.
መልሶችዎን ለማጣራት ማዳመጥዎን ይቀጥሉ። በመቀጠል ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያወዳድሩት።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በደህና መጡ። አብረናችሁ አዘጋጆች እኔ ዘሩባቤል እና ሳም ነን።
Sam
Hello, everybody. Welcome!
ዘሩባቤል
በዚህ ዝግጅት ስልክ እንዴት መደወል እንደሚቻል እናያለን። በሁለት ሰዎች መካከል የሚደረግ አጠር ያለ የስልክ ልውውጥን በማዳመጥ እንጀምር። ሁሉንም ነገር ባይረዱ ስጋት አይግባዎት፤ ቆየት ብለን እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ደዋዩ ፒተር ለማን እንደደወለ እና እርሷንም አግኝቷት እንደሆነ ያዳምጡና ይወስኑ።
Melissa’s mother
Hello?
Peter
Hello, is Melissa there, please? It’s Peter.
Melissa’s mother
Sorry, she's not here at the moment. Can I take a message?
Peter
It's ok. I'll call back later.
ዘሩባቤል
አዳመጡ? ፒተር ሜሊሳን ለማናገር ነው የደወለው፤ ቢሆንም አላገኛትም። ስለዚህ ሳም ስልክ ለመደወል የምንጠቀምበትን ቋንቋ እንመልከት?
Sam
Good idea!
ዘሩባቤል
ስለዚህም ፒተር የሜሊሳን እናት የጠየቃቸው የመጀመሪያው ነገር ሜሊሳ ቤት ውስጥ እንዳለች ነው፤ ይሄንንም ያደረገው እንዲህ በማለት ነው፤ ‘Is Melissa there, please?’
Sam
Yes, we make this question with ‘is’, the person’s name, and ‘there’. Let’s practise it together! Repeat after me:
Is…
…there…
Is Melissa there, please?
Is Susan there, please?
Is Mark there, please?
ዘሩባቤል
አሁን ደግሞ ፒተር ራሱን እንዴት እንዳስተዋወቀ እንይ፤ ‘I’m Peter’ አለ ወይንስ ‘It’s Peter’?
It’s Peter.
Sam
He says ‘It’s’.
ዘሩባቤል
አዎ፥ ይህ በስልክ ከሚደረግ የስልክ ልውውጥ ጋር ብቻ የሚያያዝ ነው። ራሳችን በአካል ስናስተዋውቅ ‘I’m…’ ወይንም ‘My name’s…’ ነው የምንለው።
Sam
…But on the telephone, ‘it’s’.
ዘሩባቤል
አሁን የሜሊሳ እናት ምን እንዳሉ እናዳምጥ፤ አንድ ነገር ለማድረግ ጠየቁ?
Sorry, she's not here at the moment. Can I take a message?
ዘሩባቤል
አዎ፤ መልዕክት ለመቀበል ‘take a message’ ብለው ነው የጠየቁት። ‘Can I…’ በንግግሩ ውስጥ ‘take’ ከተባለው ግስ ጋር ነው የተጠቀሙት።
Sam
But what did Melissa’s mother say before that?
ዘሩባቤል
አዎ፥ ‘sorry’ ይቅርታ ‘she’s not here’ የለችም ‘at the moment’ በአሁኑ ሰአት ነው ያሉት።
It's ok. I'll call back later.
ዘሩባቤል
አላለም፥ ‘It’s ok’ ነው ያለው፤ ይሄም ግድየለም ይቅርብኝ፥ ግን አመሰግናለሁ የማለት ሌላ መንገድ ነው። ከዚያ ‘l’ll call back later’ ቆይቼ እደውላለሁ ነው ያለው። ይህ አረፍተ ነገር የተዋቀረው ከ ‘I’ እና ‘will’ ሲሆን አንድ ላይ ሆነው ‘I’ll’ ይፈጥራሉ፤ እርሱንም ተከትሎ ግስ ይመጣል፤ እዚህ የመጣው ግስ ‘call back’ ነው።
Sam
Let’s practise all together! Repeat after me:
I’ll...
I’ll call...
I’ll call back later.
Well done! You sound very natural now.
Now it’s time for you to have some practice!
ዘሩባቤል
አዎ! ስልክ እየደወሉ እንደሆነ አስቡ፤ ራስዎን እንዴት ነው እንደሚያስተዋውቁት? ያስታውሱ ‘I’m’ አይደለም፤ ሳም የራሷን ስም ተናግራ ስታስተዋውቅ ከሰሙ በኋላ ስምዎን ይጠቀሙ ።
Sam
It’s Sam.
ዘሩባቤል
ጥሩ! አሁን ለሜሊሳ እየደወሉ ነው፤ ስልኳን ግን አታነሳም። ምን ጥያቄ ይጠይቃሉ? ቀጥሎ ሳም ትነግርዎታለች።
Sam
Is Melissa there, please?
ዘሩባቤል
Good! አሁን ለጥያቄዎ መልሱን ያዳምጡ።
Sorry, she's not here at the moment. Can I take a message?
ዘሩባቤል
አመሰግናለሁ ግን በኋላ እደውላለሁ ለማለት ምን ይላሉ? የመጀመሪያው ክፍል በ ‘it’s’ ሲጀምር ሁለተኛው ክፍል ደግሞ በ ‘I’ll’ ይጀምራል።
Sam
It's ok. I'll call back later.
ዘሩባቤል
Great! አሁን ስልክ እንዴት መደወል እንደሚቻል አውቀዋል።
Sam
Yes, congratulations! Please join us next week for another episode of How do I… Bye!
ዘሩባቤል
Bye!
Learn more!
1. የተደወለለት ሰው ስልኩን ካላነሳ፤ ስለምፈልገው ሰው እንዴት መጠየቅ ችላለው?
ሁለት አማራጮች አሉ።
Is ____ there, please?
Can I speak to _____, please?
2. ለዚህ ጥያቄ መልስ ሊሆኑ የሚችሉ ሁለቱ አማራጮች የትኞቹ ናቸው?
የተደወለለት ሰው ከሌለ፤ የሚሰጥዎት መልስ ይህ ይሆናል ‘He/She’s not here at the moment’. የተደወለለት ሰው ካለ፤ ስሞትን እንዲነግሩት ‘Who’s speaking?’ ወይም ‘Who’s calling?’ ብሎ ይጠይቆታል
3. በስልክ ንግግር ወቅት ‘I’m ______’ ወይም ‘My name’s ______’ መጠቀም እንችላለን?
ትክክለኞቹ ራስን የማስተዋወቂያ መንገዶች እነዚህ ናቸው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ለስልክ ሲሆን ‘It’s ______’ እንጠቀማለን።
4. በዚህ ክፍል ‘Can I…?’ የሚጠቀሙ ሁለት ጥያቄዎች አሉ። ተመሳሳይ ናቸው?
‘Can’ በጣም ጠቃሚና ብዙ ትርጉሞች ያሉት ቃል ነው። ጥያቄ ለመጠየቅ ሊጠቅም ይችላል፤ ለምሳሌ ‘Can I speak to ______, please?’ እና እርዳታ ለማቅረብም ይጠቅማል፤ ለምሳሌ ‘Can I take a message?’። ጥያቄው የሚመሰረትብት መንገድ ግን አንድ አይነት ነው። ‘Can I...’ + ግስ
ስልክ እንዴት መደወል እችላለሁ?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ድጋፍ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ፍንጭ
ለመጠየቅ ‘can’ ወይም ‘is’ ብለው መጀመር ይችላሉ።Question 1 of 3
ድጋፍ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ፍንጭ
ሁለት ትክክለኛ አማራጮች አሉ። አንዱ አዎ ሲል ሌላኛው ደግሞ አይደለም ይላል።Question 2 of 3
ድጋፍ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ፍንጭ
በስልክ ማውራት በአካል ከመገናኘት ይለያል።Question 3 of 3
Excellent! Great job! መጥፎ እድል ነጥብ አስመዝግበዋል :
Who’s speaking, please? Join the conversation on our Facebook group!
ውይይቱን በፌስቡክ ገጻችን ይቀላቀሉ።
Join us for our next episode of How do I… when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ጠቃሚ ቋንቋዎችን ለመማርና የማዳመጥ ክህሎትዎን በልምምድ ለማዳበር ቀጣዩን How do I… ዝግጅታችንን ይከታተሉ።
Session Vocabulary
Hello?
ሰላም
Hello, is ______ there, please?
ሰላም፥ እባክዎ ______ ይኖራል?
Sorry, he/she's not here at the moment.
ይቅርታ ለጊዜው ______ የለም/የለችም።
Can I take a message?
መልዕክት መቀበል እችላለሁ?
It's ok. I'll call back later.
ችግር የለውም። ቆይቼ እደውላለሁ።
Hello, can I speak to ______, please?
ሰላም፤ ከ______ ጋር መነጋገር እችላለሁ?
Yes. Who’s speaking, please?
አዎ። እርስዎን ማን ልበል?
It’s ______.
እኔ ______ ነኝ።